ዜና እረፍት

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

ራእይ አይሞትም
የታላቁን የታሪክ ተመራማሪ፣ ደራሲና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያምን ዜና እረፍት የሰማነው ጥልቅበሆነ ሐዘን ነው።

ፕሮፌሰር መስፍን ዕድሜያቸውን ሙሉ ትውልድ ሃገሩን እንዲያውቅ፣ በኢትዮጵያዊ ማንነቱ እንዲኮራ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ በሚያምንበት በጎ ሥራ የማያወላውል አቋም እንዲኖረውና ያለፍርሃት እንዲቆም ራሳቸው አርአያ በመሆን በተግባር ያስተማሩ ጀግና አባት ነበሩ።

የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ ሃገራችን ኢትዮጵያ ጋሽ መስፍንን የመሰለ ታላቅ ሰው በማጣቷ እጅግ አድርገን ያዘን መሆናችንን ለመላው ዘመዶቻቸውና ደጋፊዎቻችን ለመግለፅ እንወዳለን።

እግዚአብሔር ለቤተሰቦቻቸውና ለሚወዳቸው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን እንዲሰጥልን ከልብ እንመኛለን።

የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ 

© Copyright 2020 ESFNA - All Rights Reserved