የእግር ኳስ አባወራውን ተሠናበትነው

በኢትዮጰያ የእግር ኳስ ታሪክ ከሚወሡ ስኬቶች መካከል የሚጠቀሠው ሦስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ድል ነው።ይህ በሀገሪቱ አንድ ለእናቱ የሆነው ድል ሲነሣ ትውልድ ከሚጠቅሳቸው የቡድን አባላት መካከል ሉቺያኖ ባሳሎ ቀዳሚው ነበር።ይህ ድንቅ እግር ኳሠኛ በወቅቱ የስፖርት ቤተሠቦች ዘንድ በችሎታው የሚደነቅ የቡድን ስራ ላይ ከፍተኛ ሚና የነበረው ስፖርተኛ ነበር።

ከአስመራ የጀመረው የእግር ኳስ ህይወቱ ወደ ድሬዳዋው ጥጥ ማህበር ከዛም ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ተጫዋችነት እና አሠልጣኝነት የተሻገረ የእግር ኳስ ስኬቶቹ የሉቺያኖ መታሠቢያ ነው።

በሦሥተኛው የአፍሪካ ዋንጫ በዘጠኝ ቁጥር ሚና ተጠቃሽ የነበረው ሉቺያኖ ከመንግስቱ ወርቁ ጋር የነበረው ጥምረት በጣሙን የሚደነቅ ነበር።የወቅቱ የቡድኑ አሠልጣኝ የተከበሩ አቶ ይድነቃቸው ተሠማ ለሉቺያኖ የተለየ አክብሮት እንደነበራቸውም ታሪክ ይዘክራል።

በጎርጎሪያው የዘመን ቀመር 1962 ኢትዮጵያን የወከለው ቡድን አምበል የነበረው እና በግማሽ ፍፃሜ ቱኒዚያ ላይ ሁለት ያገባው ሉቺያኖ በውድድሩ ባሳየው ድንቅ ብቃት የውድድሩ ኮከብ ተብሏል።በ2006 ካፍ የ50 ዐመቱ ምርጥ እግር ኳሰኞችን ሲመርጥ ሉቺያኖም ተካቷል።ከወንድሙ ኢታሎ ጋር ለኢትዮጵያ ብ/ቡድን በጋራ የተጫወተው ሉቺያኖ ለኢትዮጵያ ቡ/ቡድን በርካታ ጨዋታዎችን ተሠልፎ ተጫውቷል ።

በቅ/ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለቡም በአሠልጣኝነት ዘመን ተሻጋሪ ታሪክን መስራት ችሎ ነበር።ሉቺያኖ በጥጥ ማህበር በነበረው ቆይታ 10 ዕጥፍ ከሌላው የተለየ ክፍያ ይከፈለው እንደነበርም ታሪክ ያስታውሳል።ሉቺያኖ በቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ቢሸለምም በቀይ ሽብር ወቅት እስር ቀምሷል።የኢትዮጵያ ቡድንንም የማሠልጠን ዕድል እንደነበረውም ታሪክ ያወሳል።ሉቺያኖ በጣልያን የወጣቶች ማሠልጠኛ አቋቁሞ ይሠራም ነበር።

ሉቺያኖ በተወለደ በ87 ዐመቱ በሚኖርበት ጣልያን ሀገር ህይወቱ አልፏል።ሉቺያኖ ባሳሎ በ1992 ከወንድሙ ኢታሎ ጋር በጋራ በመሆን የኢ ኤስ ኤፍ ኤን ኤ የክብር እንግዳ እንደነበሩ ይታወሳል።

ነብስ ይማር

Join us on our 39th
Annual Sports & Cultural Event!