ወርቃማው የስፖርት ድምፅ ተዘጋ

የስፖርቱ አንደበት ጉምቱው ሠው ከኢትዮጵያ እስከ አፍሪካ የስፖርትና ስፖርተኞች ልሣን።በበርካታ ኦሎምፒኮች የቡድኑ የጀርባ አጥንት እና አስተባባሪ ኢትዮጵያ በታሪኳ መስመር በ2001 ለዐለም ወጣቶች ዋንጫ ስትዘልቅ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል።አንድ ሆነው እንደብዙ ለሀገሪቱ ስፖርት የለፉ የደከሙ ጋዜጠኞች በሙያዊ ብቃት ከፍ እንዲሉ ከሚያደርጉት ሙያዊ ድጋፍ ባለፈ የጋዜጠኛው መብት እንዲከበር የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ሀሣብ ጠንሳሽ እና የመጀመሪያው ፕሬዘዳንት፣በጉለሌ ተወልደው በፒያሳ ልጅ መፅሀፍ ብዙ የነገሩን የስፖርቱ ታላቅ ሠው ፍቅሩ ኪዳኔ በሀገሪቱ ብሎም በአፍሪካ እና በዐለሙ ታላቅ ስም ያላቸው የስፖርት ሠው ህልፈት እጅግ ትልቅ ስብራት ነው።

በ1935 በአ.አ የተወለዱት ፍቅሩ ኪዳኔ አባታቸው የስፖርት ሠው ስለነበሩ በልጅነታቸው ከአባታቸው ጋር ሜዳ በመዋል ስፖርትን መውደድ ተለማመዱ። የስፖርት መምህር ከዚያምበ1957 የስፖርት ጋዜጠኛ ሆኑ ።ከዚህ በኋላም ፍቅሩ የተለያዩ ዘገባዎችን ያቀርቡ ጀመር በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው ኮሜንታተር በመሆንም ኢትዮጵያ ከ ሱዳን ያደረጉትን ጨዋታ አስተላልፈዋል።በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ፣እግር ኳስ፣ብስክሌት ፌደሬሽኖች በተለያየ ሀላፊነት ሀገራቸውን አገልግለዋል።በአህጉራዊው መድረክም የካፍ ተወካይ በመሆን አገልግለዋል።

ጋሽ ፍቅሩ ኪዳኔ በሀገሪቱ የስፖርት ጋዜጠኝነት ብዙም ባልተስፋፋበት ወቅት በተለያዩ ጋዜጦች በመፃፍ ሙያውን አለማምደዋል። ከሀገር ከወጡም በኋላ በፈረንሳይ ተነባቢ በሆነው ለኢኪፕ ጋዜጣ ይፅፉ ነበር።ኋላ ላይም የራሳቸው የሆነ በእንግሊዝኛ እና ፈረንሳይኛ የሚታተም  ጋዜጣን ጀምረው ነበር። በዐለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የሚታተመው መፅሄት ዋና አዘጋጅ በመሆንም አገልግለዋል። ለቢቢሲ፣ቪኦኤ፣ዶቼቨለ እና ፍራንስ ኢንተርናሽናል ዘጋቢ በመሆንም ሠርተዋል። የሰሜን አሜሪካ ኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌደሬሽን በ2013 እ.ጎ.አ የመጀመሪያ ዲቪዥን ዋንጫን ለሀገሪቱ ስፖርት ላበረከቱት አስተዋፅኦ መታሠቢያ ይሆን ዘንድ
በስማቸው ሠይሞ እንደነበር ይታወሳል።

ድርጅታችን የሰሜን አሜሪካ ኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌደሬሽን  ለሀገራቸው ስፖርት እስከ ዕለተ ሞታቸው በደከሙት አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ ህልፈት የተሠማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሠቦቻቸው እና መላ ኢትዮጵያውያን መፅናናትን ይመኛል።

Join us on our 39th
Annual Sports & Cultural Event!