ዓሊ ብራ ነብስ ይማር

የምስራቁ ኮከብ የኢትዮጽያ ሙዚቃ አርበኛ አሊ ብራ በኢትዮጵያ ዘመናዊ የሙዚቃ ታሪክ ስማቸው በጉልህ ከሚነሱት መካከል ግንባር ቀደሙነው።
ዓሊ ለ ስድስት አስርት አመታት በሙዚቃው ፍቅርን፣እኩልነትን፣ሠብአዊነትን ሠብኳል።ከድሬደዋ የተነሣው የአሊ የሙዚቃ ህይወት በወርቃማ ድምፁ ታግዞ ዘመናትን ከፍ እያለ ተጉዟል።
በድሬዳዋ ከተማ በ1940 የተወለደው ዓሊ ገና በ14 ዐመቱ አፈረን ቀሎ የሙዚቃ ብድንን በመቀላቀል የህይወት ጥሪው ወደሆነው የሙዚቃ ስራ ገብቷል።ወላጆቹ ዓሊ መሀመድ ሙሳ ብለው የመዝገብ ስም ቢሠጡትም መድረክ ላይ ለመጀመሪያ ግዜ ባቀነቀነው ብራ ዳህ ቢርሄ ሙዚቃ ምክንያት ዓሊ ብራ የሚለው ስያሜን አግኝቶ እስከ ህልፈተ ህይወቱ ተጠርቶበት አልፏል።
አማሌሌ፣ማልቱ አዳን ኑባሴ እና በርካታ ዘመን ተሻጋሪ የሆኑ ሙዚቃዎች ያቀነቀነው ዓሊ ከኦሮምኛ ባሻገር በአማርኛ ፣ሀደርኛ፣አፋርኛ፣ሶማልኛ፣አረብኛ እና በተለያዩ ቋንቋዎችም ሙዚቃን ተጫውቷል።
ዓሊ ከተለያዩ ተቋማትም የተለያዩ ሽልማቶችን ያገኘ ሲሆን የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲም የክብር ዶክትሬት ሠጥቶታል። በክብር ዘብ የሙዚቃ አባል የነበረው ዓሊ ከራሱ ባለፈ ተወዳጅ የሆኑ ዜማዎችን ለመሀመድ አህመድ፣ለእሣቱ ተሠማ እና ለሌሎች ሙዚቀኞች አበርክቷል።
ዓሊ ከድምፃዊነቱ ባሻገር የሙዚቃ መሣሪያዎችንም ይጫወት ነበር። ዓሊ መሀመድ ሙሳ  ወይም ዓሊ ብራ በገጠመው ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በተወለደ በ75 ዐመቱ ከዚህ ዐለም በሞት ተለይቷል።
ፌደሬሽናችን በዚህ ታላቅ የጥበብ ሠው ህልፈት የተሠማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል። ለቤተሠቦቹ፣ለአድናቂዎቹ እና መላ ኢትዮጵያውያን መፅናናትን ይመኛል።

Join us on our 39th
Annual Sports & Cultural Event!