ዳዊት ከበደ ወየሳ በድንገት አለፈ

ውሸት ያላቆማቸው ሀሳቦች አምባገነኖች ያልቀየሩት ማንነት በሞት ተረታ።እርሱ በብዕሩ የተበደለችው የወላድ መካን የሆነችው ሀገሩን ከበዝባዦች ለማላቀቅ ሞክሯል።
እውነት ስትቀበር የሀሠት ወገን ሲበረታ ከውሸት አልወግንም በማለት የግፈኞችን ፅዋ ቀምሷል ተደብድቧል፣ታስሯል ድቅድቅ ባለ ጨለማ ውስጥ መርፌን የመፈለግ ያህል ርቃ ለነበረችው እውነት ድምፅ ሆኗል።
ዳዊት ከበደ ወየሳ በአ.አ ከተማ ቄራ የተወለደ ሲሆን የነፃው ፕሬስ ላይ ከተሣተፉ ጥሩ አሻራቸውን መልካም ስዕብናቸውን ካሣረፉ ባለሙያዎች ውስጥ ይጠቀሳል።
በ1961 ዓ.ም ታህሳስ 19 ወደዚህች ምድር የመጣው ዳዊት በኢትዮጵያ በነበረበት ግዜ የፊያሜታ ጋዜጣን ያሣትም የነበረ ሲሆን በለገዳዲ ሬድዮም ሠርቷል።
የመንግስትን በደል በብዕሩ መንቀፉ በወቅቱ መንግስት ጥርስ ውስጥ የከተተው ዳዊት ወደ አሜሪካ በማቅናት በአትላንታ ኑሮውን በማድረግ በአድማስ እና ትንሳኤ ሬድዮ እንዲሁም ድንቅ መፅሄት በመስራት ሙያዊ አሻራውን አሳርፏል።
ዳዊት ሠው አከባሪ ሙያውን አክባሪ የነበረ ሲሆን ከሚኖርበት አትላንታ ወደ አ.አ በሄደበት አጋጣሚ ማለፉ አስደንጋጭ ሆኗል።
የፌደሬሽናችን ወዳጅ ተባባሪ በነበረው ዳዊት ከበደ ወየሳ  ድንገተኛ ህልፈት የተሠማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን።
በሠሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርት እና ባህል ፌደሬሽን ለቤተሠቡ አና ለመላው ኢትዮጵያዊ መፅናናትን ይመኛል።

Join us on our 39th
Annual Sports & Cultural Event!