ዳዊት ከበደ ወየሳ በድንገት አለፈ

ውሸት ያላቆማቸው ሀሳቦች አምባገነኖች ያልቀየሩት ማንነት በሞት ተረታ።እርሱ በብዕሩ የተበደለችው የወላድ መካን የሆነችው ሀገሩን ከበዝባዦች ለማላቀቅ ሞክሯል። እውነት ስትቀበር የሀሠት ወገን ሲበረታ ከውሸት አልወግንም በማለት የግፈኞችን ፅዋ ቀምሷል ተደብድቧል፣ታስሯል ድቅድቅ ባለ ጨለማ ውስጥ መርፌን የመፈለግ ያህል ርቃ ለነበረችው እውነት ድምፅ ሆኗል። ዳዊት ከበደ ወየሳ በአ.አ ከተማ ቄራ የተወለደ ሲሆን የነፃው ፕሬስ...

ዓሊ ብራ ነብስ ይማር

የምስራቁ ኮከብ የኢትዮጽያ ሙዚቃ አርበኛ አሊ ብራ በኢትዮጵያ ዘመናዊ የሙዚቃ ታሪክ ስማቸው በጉልህ ከሚነሱት መካከል ግንባር ቀደሙነው። ዓሊ ለ ስድስት አስርት አመታት በሙዚቃው ፍቅርን፣እኩልነትን፣ሠብአዊነትን ሠብኳል።ከድሬደዋ የተነሣው የአሊ የሙዚቃ ህይወት በወርቃማ ድምፁ ታግዞ ዘመናትን ከፍ እያለ ተጉዟል። በድሬዳዋ ከተማ በ1940 የተወለደው ዓሊ ገና በ14 ዐመቱ አፈረን ቀሎ የሙዚቃ ብድንን በመቀላቀል የህይወት ጥሪው...

ወርቃማው የስፖርት ድምፅ ተዘጋ

የስፖርቱ አንደበት ጉምቱው ሠው ከኢትዮጵያ እስከ አፍሪካ የስፖርትና ስፖርተኞች ልሣን።በበርካታ ኦሎምፒኮች የቡድኑ የጀርባ አጥንት እና አስተባባሪ ኢትዮጵያ በታሪኳ መስመር በ2001 ለዐለም ወጣቶች ዋንጫ ስትዘልቅ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል።አንድ ሆነው እንደብዙ ለሀገሪቱ ስፖርት የለፉ የደከሙ ጋዜጠኞች በሙያዊ ብቃት ከፍ እንዲሉ ከሚያደርጉት ሙያዊ ድጋፍ ባለፈ የጋዜጠኛው መብት እንዲከበር የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ሀሣብ...

አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ

የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌዴሬሽን በአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን። ማዲንጎ በየአመቱ በሰሜን አሜሪካ በምናዘጋጀው የስፖርትና የባህል ዝግጅት ላይ በመገኘት ድንቅ የሙዚቃ ስራዎቹን ለህዝብ ያደረሰና ከፌደሬሽናችን ጋር መልካም የስራ ግንኙነት የነበረው ወጣት ከያኒ ነበር። በአርቲስት ማዲንጎ ድንገተኛና ያልታሰበ ህልፈት በሀዘን ላይ ላላችሁ ወዳጅ...

የእግር ኳስ አባወራውን ተሠናበትነው

በኢትዮጰያ የእግር ኳስ ታሪክ ከሚወሡ ስኬቶች መካከል የሚጠቀሠው ሦስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ድል ነው።ይህ በሀገሪቱ አንድ ለእናቱ የሆነው ድል ሲነሣ ትውልድ ከሚጠቅሳቸው የቡድን አባላት መካከል ሉቺያኖ ባሳሎ ቀዳሚው ነበር።ይህ ድንቅ እግር ኳሠኛ በወቅቱ የስፖርት ቤተሠቦች ዘንድ በችሎታው የሚደነቅ የቡድን ስራ ላይ ከፍተኛ ሚና የነበረው ስፖርተኛ ነበር። ከአስመራ የጀመረው የእግር ኳስ ህይወቱ ወደ ድሬዳዋው ጥጥ ማህበር ከዛም...