2025 Guests Of Honor
Each year, ESFNA invites individuals that have excelled in sports in Ethiopia in the past. From soccer players to long distance runners that have made the proud nation even prouder. Besides sports figures, ESFNA also honors Ethiopians in the social and art field. If it were not for the invitation of ESFNA, most of these heroes would not have had the opportunity to visit the United States.

ዘነበ አርጋው (ቮልቮ)
የክብር እንግዳ
የትውልድ ዘመን፡- 1949 ዓ.ም
የእግር ኳስ ተሳትፎ ያደረግኩባቸው ክለቦች፡-
- አየር ኃይል (ንብ) ከ1969-1970 ዓ.ም
- የኢሰማው (ወደፊት) ከ1971-1974 ዓ.ም
- መድን ድርጅት ከ1975-1978 ዓ.ም
- ብሔራዊ ቡድን ከ1972-1978 ዓ.ም
1- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ1972 ዓ.ም ለ12ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከዛምቢያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ለነበረው የመጀመሪያ ማጣሪያ ግጥሚያ ዝግጅት ብሔራዊ ቡድኑን ተቀላቀልኩ (ተመረጥኩ) ማጣሪያውን ማለፍ አልተቻለም (ታምራት ማሞና መሠረት ኦላና) ናይሮቢ ላይ ቀሩ፡፡
2- በ1974 ዓ.ም ሊቢያ ላይ ለተዘጋጀው 13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከመጀመሪያው ማጣሪያ ጀምሮ የመጀመሪያውን በፎርፌ ሁለተኛውን ማጣሪያ ሩዋንዳን በደርሶ መልስ በማሸነፍ ሶስተኛውንና የመጨረሻውን ማጣሪያ የጊኒን ብሔራዊ ቡድን በደርሶ መልስ በማሸነፍ የውድድሩ ተሳታፊ የነበረው ቡድን አባል ነበርኩ፡፡ (አፈወርቅ ጠናጋሸው፣ አቦነህ ማሞ፣ ንጉሴ አስፋው፣ ሸዋንግዛው ተረፈ፣ አያሌው መንገሻ፣ ዳዊት ኃይለአብ፣ ግርማ ከበደ) ከጊኒ መልስ አይቮሪኮስት አቢጃን ላይ ቀሩ፡፡
እግር ኳስን የበለጠ መጫወት በምችልበት ዘመን ባጋጠመኝ የመገጣጠሚያ ሕመም ችግር ምክንያት በ1978 ዓ.ም መጫወት አቆምኩ፡፡
የዘመን አቆጣጠሩ በሙሉ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር መሆኑ ይታወቅ፡፡

Kasahun Gebrehiwot
የክብር እንግዳ
እኔ ካሣሁን ከአባቴ ከአቶ ገ/ሕይወት ከበደ ከእናቴ ከወ/ሮ ብዙነሽ ዓለሙ በ1948 ዓ/ም አዲስ አበባ ልዩ ስሙ ካዛንቺስ ተወለድኩ ዕድሜዬ ለትምህርት ሲደርሰ የአፄ ምንሊክ ቤተመንግሥት ጊቢ ውሰጥ ፌደል ቆጠርኩ አንደኛደረጃትምህርቴን ኢትዮጵያ አንድነት መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ዑራኤል መለሰተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን አሰፋ ወሰን አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ እየተማርኩ በልጅነቴ ባደረብኝ የእግርኳስ ፍቅር በ1964 ዓ/ም ዳኘው እግርኳስ ቡድን ህጻናት ቡድን ተመዘገብኩ በዚያው ዓመት ውሰጥ የኢትዮጵያ ት/ቤቶች የሰፓርት በዓል በእግርኳስ ተመረጥኩ ከግርማዊ ቀዳማዊ ሀይለ ሥላሴ እጅ ዋንጫና የወርቅ መዳሊያ ተሸለምን በ1966 ዓ/ም ለዳኘው ዋናው የእግርኳስ ቡድን መጫወት ጀመርኩ በ1967እና በ1968 ዓ/ም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ተስፋ ቡድንና ዋናው ቡድን ተመርጬ ተጫወትኩ በ1969 ዓ/ም በነበረው የኢትዮጵያ ሻምፒዮና ለሸዋ ምርጥ ተመረጥኩ ዋንጫና የወርቅ መዳሊያ እንዲሁም የሸዋ እግርኳስ ፌዴሬሽን 12ግራም የወርቅ ቀለበት ሽልማት አገኘን በ1970 ዓ/ም ወደኦሜድላ እግርኳስ ቡድን ዝውውር አደረግሁ በዚሁ ዓመት ቡድኑ የኢትዮጵያ ሻፒዮና ሲሆን የዋንጫና የወርቅ መዳሊያ ተሸላሚ ሆነናል በ1971 ዓ/ም ለአፍሪካ የክለብ ሻፒዮና ኦሜድላ ከታዛኒያው ፓንአፍሪካ ጋር ዳሬሰላም ላይ በተደረገው የእግርኳስ ጨዋታ በኢትዮጵያ እግርኳስ ክለቦች ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሀገር ውጭ አሸናፊ ሆኖ ሲመለሰ አንዱ የክለቡ ተጫዋች ነበርኩ በ1972 ዓ/ም ኦሜድላ ለኢትዮጵያ እግርኳስ ሻምፒዮና ከትግል ፍሬ ጋር ተጫውቶ የብር መዳሊያ ተሸልመና ል ሌላ በዝርዝር ያልጠቀሰኳቸው ብዙ ዋንጫና ልዩ ሸልማት አግኝተናል ለምሳሌ በእናት ሀገር ጥሪ ፈጣሪ ነብሱን ይማረው ከአሰልጣኝ አስራት ሐይሌ ጋር ከ2014 ዓ/ም ጀምሮ ለአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ኮሚቴ በመሆን ነፃ አገልግሎት እየሰጠሁ እገኛለሁ በግል የሕይወት ታሪክ ደግሞ ከባለቤቴ ከወ/ሮ ሐረገወይ በየነ በሕግ ተጋብተን ለ39 ዓመት ስንኖር የአንድ ሴት ልጅ የአራት ወንዶች ልጆች ወላጆች ነበርን ባለቤቴ ሐረገወይን የተወለደችው አዲስ አበባ ልዩ ሰሙ ሆላንድ ኤምባሲ አካባቢ ነው የምድር ባቡር የሴቶች እግር ኳስ ተጨዋች የኦሜድላ የእጅ ኳስ ተጫዋች ፓሊስ ውሰጥ በስፖርት ሲቪል ስራተኛ በመሆን የኦሜድላ የወንዶች መረብ አሰልጣኝ በመቀጠል በራሳቸው የግል ጥራት ባቋቋሙት የሴቶች መረብ ኳስ አሰልጣኝ የኢትዮጵያ ቢሔራዊ የሴቶች የመረብ ኳስ አሰልጣኝ በመሆን ቡድኑን የተለያዩ የአፍሪካ አገሮች በመሄድ ብዙ ወድድሮችን አድርጓል የመረብ ኳስ ከፍተኛ የአሰልጣኞች ሰልጠና FiVB የሚሰጠውን በኡጋንዳ በግብፅ ወስደዋል ወ/ሮ ሐረገወይን በድንገተኛ ህመም ፓሊስ ሆስፒታል በሞት ተለይተዋል በዚህ ሀዘን ላይ የሰፓርት ቤተሰብ ላደረገው መጽናናት ከልብ አመሰግናለሁ።
Previous Dignitaries

Rep. Maxine Waters

Rep. Mike Honda

Rep. John Lewis

Rep. Karen Bass

Isiah Leggett
