2023 Guests Of Honor
Each year, ESFNA invites individuals that have excelled in sports in Ethiopia in the past. From soccer players to long distance runners that have made the proud nation even prouder. Besides sports figures, ESFNA also honors Ethiopians in the social and art field. If it were not for the invitation of ESFNA, most of these heroes would not have had the opportunity to visit the United States.

Bekeri Adem
Guest of Honor
በከሪ አደም በጠንካራ ምቶቹ በርካታ ጎሎችን ከማስቆጠሩም በለይ በርካታ ተጫዋቾችን የጎዳው የድሬ ኮከብ የምስራቁ አንበሳ በከሪ አደምን በወፍ በረር ላስቃኛችሁ።
ገና የ6 ዐመት ህፃን እያለነው በእግር ኳስ ፍቅር የተለከፈው በከሪ ወንድሙ እግር ኳስ ይጫወት ስለነበር እርሡም ወደ ኳስ በመሣብ የቀፊራ ኮከብ እግር ኳስ ቡድን ሲቋቋም የቡድኑ አባል ሆነ።ከዛም እድሜው ትንሽ ከፍ ሲል በ10 ዐመቱ ገደማ ወደ ምድር ባቡር ቡድን በመግባት የቡድኑ ተጫዋች ሆነ የመጀመሪያዎቹን አመታት ወጣት ቡድን የቆየው በከሪ ወደ ዋናው ቡድን አደገ።
በምድር ባቡር በዘጠኝ ቁጥር ሚና መጫወት የጀመረው በከሪ በክለቡ እያሣየ በነበረው ብቃት በመሣብ የብሄራዊ ቡድኑ ዐይን ውስጥ በመግባት ለብሄራዊ ቡድን ተጠራ።
ከ10ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አንስቶ ለብሄራዊቡድን መሠለፍ የጀመረው በከሪ በተለያዩ ውድድሮች ኢትዮጵያን ወክሏል።

Eshetu Tura
Guest of Honor
በመሠናክል ውድድር ሀገራችንን ካስጠሩ ቀደምት ስፖርተኞች አንዱ ናቸው።
በ3000 ሜትር መሠናክል እንዲሁም በ5000 ሜትር በተለያዩ መድረኮች ሀገራቸውን በዐለም አቀፍ መድረክ አስጠርተዋል።የአበበ ቢቂላ እና ማሞ ወልዴን ዝና በመስማት ወደ አትሌቲክሱ የገቡት ሻ/ል እሸቱ ቱራ
ከተወዳዳሪነት ወደ አሠልጣኝነት በመግባትም ስኬታማ መሆን ችለዋል።

Loza Abera
Special Guest
ትውልድ እና እድገቷ የከምባታ ጠምባሮ ዞን ዱራሜ ከተማ ነው።እቤታቸው ደጃፍ የነበረው ሌሊሶ ሜዳ ከልጅነቷ አንስቶ በእግር ኳስ እንድትሳብ አድርጓታል።
ሎዛ አበራ በቴሌቭዥን የብራዚላዊቷን ማርታ ታሪክ ስትመለከት ውስጧ ያለው የእግር ኳስ ፍቅር የበለጠ እነደደ መጣ።ትምህርት ቤት ስትሄድ በአንድ እጇ ደብተር በሌላው ኳስ ይዛ ነበር ምትሄደው ሱቅ ስትላክም ኳስ እያንከባለለች ነበር የምትሄደው ።
ሎዛ አበራ ወደ ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ህይወት እንድትገባ መነሻ የሆናት በ2004 የከምባታ ዞን ሻምፒዮና ነው።ውድድሩ በድራሜ ሲካሄድ ዱራሜን ወክላ የተጫወተችው ሎዛ ኮከብ ጎል አግቢ ሆነች።የውድድሩ አዘጋጅ የነበሩት ዶክተር ቦጋለች የብሄራዊ ቡድን ቱታ እና የአንገት አምባር ሸለምዋት አምባሩ ላይ ዊመታ የሚል ፅሁፍ የተፃፈበት ሲሆን ትርገሙም ስኬታማነትን የሚገልፅ ነበር።በኢትዮጵያ ሻምፒዮና ደቡብ ክልልን የወከለችው ሎዛ ኮከብ ግብ አግቢ ሆና አጠናቀቀች።ወደ ክለብ የመግባት ዕድሉን አገኘች ሀዋሳ ከነማ የመጀመሪያ ክለቧ ሆነ።
Dignitaries
Your content goes here. Edit or remove this text inline or in the module Content settings. You can also style every aspect of this content in the module Design settings and even apply custom CSS to this text in the module Advanced settings.

Rep. Maxine Waters

Rep. Mike Honda

Rep. John Lewis

Rep. Karen Bass

Isiah Leggett

Mayor Sam Liccardo
ESFNA’s Early Years
