We are thrilled to announce that the vibrant city of Seattle, Washington will host ESFNA’s 42nd Annual Soccer and Cultural Festival! This year’s festivities will celebrate the global unity that soccer fosters while highlighting the rich cultural diversity of the Ethiopian community. From exciting matches to spectacular cultural exhibitions, Seattle will serve as the perfect backdrop for this unforgettable annual event.
Event Highlights:
- Dates: June 28 – July 5, 2025
- Soccer Tournaments: Teams from across the US & Canada will compete for glory in an action-packed tournament.
- Cultural Showcases: Visitors will experience music, dance, art, and cuisine from various vendors, fostering a spirit of unity and inclusion.
ESFNA invites all Ethiopians and friends of Ethiopia from around the world to join us in Seattle for a celebration of soccer, culture and communty.
We sincerely apologize for the late announcement, but we hope you will come and join us in the great city of Seattle. ESFNA would like to take this opportunity to thank member teams from Toronto, Denver, Houston, Austin, Minnesota, Los Angeles and DMV area for their efforts to host this tournament.
Stay tuned for additional information and continue to check our website and social media for the latest updates and news.
ሲዓትል: ዋሽንግተን አዘጋጅ ከተማ ሆና ተመርጣለች!
የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ የ42ኛውን የእግር ኳስና ባህል ዝግጅት በደማቋ ሲዓትል: ዋሽንግተን እንደሚያዘጋጅ ሲገልፅ በከፍተኛ ደስታ ነው::
ዓመታዊው የእግር ኳስና ባህል ዝግጅት ከሰኔ ፳፩-፳፰, ፳፻፲፯ (June 28-July 5: 2025) ይካሄዳል:: በ32 ቡድኖች መካከል የሚደረገው ዓመታዊ የእግር ኳስ ውድድርን አካትቶ ኢትዮጵያውያን እንደተለመደው ባህላቸውን: ወጋቸውን: ምግብና ሙዙቃዎቻቸውን በአንድነት እየተጋሩ የሚያሸበርቁበት ሳምንት ይሆናል!
የሲዓትል ከተማ በበጋ ወራት እጅግ የሚስማማ የአየር ፀባይ ስላላት የፌዴሬሽኑን ውድድር ስታዘጋጅ ይህ አራተኛ ጊዜዋ ይሆናል:: ሲዓትል የብዙ ኢትዮጵያውያን መኖሪያ ናት:: የከተማዋ ሁለት የእግር ኳስ ቡድኖችና በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ማህበረሰቡ ጠንካራ ማህበራዊ ትስስር ያለው ነው:: ፌዴሬሽኑ የሲዓትል ከተማ ነዋሪዎች ጋራ እንደቀደሙት አመታት መልካም ጊዜ እንደሚኖረው እርግጠኛ ነው::
እንደተለመደው በዓለም ዙሪያ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን በውድድሩ ላይ እንድትታደሙ ፌዴሬሽኑ ግብዣውን በአክብሮት ያቀርባል:: Toronto, Denver, Houston, Austin, Minnesota, Los Angeles and DMV
በዚህ አጋጣሚ የቶሮንቶ: ዴንቨር: ሒውስተን : ኦስተን: ሜኔሶታ: ሎስ አንጅለስ እና በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የሚገኙትን አባላቶቻችንን ይሄንን ዝግጅት በከተማቸው ለማድረግ ያለማቋረጥ ስለደከሙ ምስጋናችንን እናቀርባለን::
ዘግይተን በማሳወቃችን አስቀደመን ይቅርታን እንጠይቃለን::
በሚቀጥሉት ቀናትና ሳምንታት ስለዓመታዊው ደማቅ ዝግጅት ተጨማሪ መረጃዎችን እናስከትላለን:: በውድድሩ ሳምንት በስቴዲየሙ ውስጥ በንግድ: በበጎ አድራጎት እንዲሁም በስፖንሰርሽፕ ጉዳዮች መሳተፍ የምትፈልጉ በድህረገፃችን ESFNA.ORG እና በሶሻል ሚዲያ ገፆቻችን ተከታተሉን::