በ39ኛው የፌደሬሽናችን ዐመታዊ ውድድር በክብር እንግድነት ተጋብዘው ለነበሩት የቀድሞ እግር ኳሰኛ በለጠ በቀለ የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ

Jan 3, 2023

በ39ኛው የፌደሬሽናችን ዐመታዊ ውድድር በክብር እንግድነት ተጋብዘው ለነበሩት የቀድሞ እግር ኳሰኛ በለጠ በቀለ የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ

News | 0 comments

ፌደሬሽናችን አቶ በለጠ የክብር እንግዳ መሆናቸው ከታወቀ ጀምሮ የሚያስፈልገውን የድጋፍ ወረቀት ቢልክም የክብር እንግዳው ቪዛ ማግኘት አልቻሉም።
የክብር እንግዳው በቦታው ቢገኙ ሊበረከትላቸው የነበረውን የገንዘብ ስጦታ ዛሬ በአ.አ በተደረገ ዝግጅት ተበርክቶላቸዋል።በእንሰት የባህል አዳራሽ በነበረው ዝግጅት ስጦታውን ከኢንስትራክተር ሠውነት ቢሻው እጅ የተረከቡት የክብር እንግዳው ፌደሬሽኑ ካለሁበት ፈልጎ የክብር እንግዳ ስላደረገኝ፤ ተሣክቶ በቦታው ባልገኝም ይህ ስጦታ ስለተበረከተልኝ አመሠግናለሁ ብለዋል።ስጦታውን በክብር እንግድነት በመገኘት ያበረከቱት ኢንስትራክተር ሠውነት ቢሻውም ፌደሬሽኑ የቀድሞ ባለውለታዎችን በማስታወስ እያደረገ ያለው ድጋፍ ይበረታታል ብለዋል።
 ከፌደሬሽናችን የተላከውን የገንዘብ ስጦታ ለክብር እንግዳው እንዲደርስ የተዘጋጀውን ዝግጅት ያስተባበሩት አንጋፋው የፌደሬሽናችን አጋር አቶ ገበያው ታከለ ናቸው።
ፌደሬሽኑ ለክብር እንግዳው 3000 ዶላር ስጦታ አበርክቷል። አቶ በለጠ በቀለ ለዳኘው፣ወሎ ምርጥ ፣ቅ/ጊዮርጊስ እና ብሄራዊ ቡድን በተጫዋችነት አገልግለዋል።
Share This